የኢትዮጵያ ምርጫ የሕዝቡን ታማኝነት፣ ትዕግስት እና ቁርጠኝነት ያሳየ ነው - የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን
19:45 03.06.2026 (የተሻሻለ: 19:54 03.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ምርጫ የሕዝቡን ታማኝነት፣ ትዕግስት እና ቁርጠኝነት ያሳየ ነው - የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን
የአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በምርጫው ዕለት የነበረው የምርጫ ድባብ በአጠቃላይ ሰላማዊ ነበር እንደነበር ገልጸዋል።
“በአብዛኞቹ በተስተዋሉ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ አሰጣጡ በሥነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ መራጮችም ያለ መስተጓጎል በቅደም ተከተል ይስተናገዱ ነበር። ይህም መራጮች ያለ ምንም እንቅፋት ድምፃቸውን እንዲሰጡ ዕድል ፈጥሯል።” ብለዋል።
በመራጮች ምዝገባ ወቅት እንደተጠቀሰው፣ በእጅ የሚከናወነውን የምዝገባ ሂደት ለማገዝ የቴክኖሎጂ መስተዋወቅ የተመዘገቡ መራጮችን ቁጥር ለመጨመር አስተዋፅኦ ሳይኖረው እንዳልቀረም ጠቁመዋል።
በተያያዘ፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ስፔሲዎሳ ዋንዲራ ካዚብዌ በሪፖርታቸው፤ ምርጫው በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ዕድገት ላይ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ገልጸዋል።
የታዛቢዎቹን መግለጫ በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X