ፕሬዝዳንት ሱሉሁ፣ ሩሲያን የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻቸው አድርገው መምረጣቸው ‘በጣም ጥሩ ምልክት’ ነው - ፑቲን

© telegram sputnik_ethiopiaፕሬዝዳንት ሱሉሁ፣ ሩሲያን የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻቸው አድርገው መምረጣቸው ‘በጣም ጥሩ ምልክት’ ነው - ፑቲን
ፕሬዝዳንት ሱሉሁ፣ ሩሲያን የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻቸው አድርገው መምረጣቸው ‘በጣም ጥሩ ምልክት’ ነው - ፑቲን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.06.2026
ሰብስክራይብ

ፕሬዝዳንት ሱሉሁ፣ ሩሲያን የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻቸው አድርገው መምረጣቸው ‘በጣም ጥሩ ምልክት’ ነው - ፑቲን

በአሥርተ ዓመታት ውስጥ (እ.አ.አ ከ1969 ወዲህ) የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ወደ ሩሲያ ያደረጉትን የመጀመሪያ ጉብኝት አስመልክቶ፣ በሩሲያው ፕሬዝዳንት እና በታንዛኒያ አቻቸው መካከል ከተካሄደው ስብሰባ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

የታንዛኒያዋ ፕሬዝዳንት ወደ ሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት “ታሪካዊ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን ለተደረገላቸው “ሞቅ ያለ አቀባበልና መስተንግዶ” ቭላድሚር ፑቲንን አመስግነዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ሱሉሁ ሶቪዬት ኅብረት እ.አ.አ በ1960ዎቹ ለአፍሪካ ነጻነት ላደረገችው ታሪካዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ ሩሲያ ዛሬም ቢሆን ለአገራቸው የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ መቀጠሏን አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

በሩሲያ እና በታንዛኒያ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ባለፈው ዓመት ከ20 እስከ 25 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

ፑቲን መጪው ጥቅምት ወር በሞስኮ በሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ታንዛኒያ በከፍተኛ የልዑካን ቡድን ደረጃ ትወከላለች ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0