አምባሳደር ለምለም ፍሥሐ በአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተደርገው ተሾሙ
17:06 03.06.2026 (የተሻሻለ: 17:14 03.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አምባሳደር ለምለም ፍሥሐ በአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተደርገው ተሾሙ
አምባሳደሯ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዛሬው ዕለት አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ለምለም ማን ናቸው?
በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ የሥራ እርከኖች ላይ ሰርተዋል፡፡
ግንቦት 2016 ዓ.ም. በቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።
እስከ አሁኑ ሹመት ድረስ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
የሹመት ደብዳቤውን የተቀበሉት የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ለአምባሳደሯ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት በማስተላለፍ ፣ ያላቸው ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ተሞክሮና መሪነት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነታቸውን ገልፀዋል።
ሁለቱም ወገኖች በቀጣይ በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X