ከሩሲያ ጋር ያለንን ‘የትራንስፖርት ትስስር ማሻሻል አለብን’ - የታንዛኒያ ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

ከሩሲያ ጋር ያለንን ‘የትራንስፖርት ትስስር ማሻሻል አለብን’ - የታንዛኒያ ባለሥልጣን

ከሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም (#SPIEF2026) ጎን ለጎን የታንዛኒያ ቱሪዝም ቦርድ ዋና ዳይሬክተር ኤፍሬም ባሎዚ ማፉሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ “ከታንዛኒያ ቱሪዝም አኳያ የሩሲያ ተጓዦችን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ወደ አገራችን መጥተው ያለምንም እንግልት ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲዝናኑ እንቀበላቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ታንዛኒያ የሩሲያ ተጓዦችን “ሊከፍሉ በሚችሉት የውጭ ምንዛሬ ዓይነት” እንዲከፍሉ በደስታ እንደምትቀበልም አክለው ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር “ከሞስኮ ወደ ዳሬሰላም የሚደረግ ቀጥታ በረራ” ወደ ታንዛኒያ የሚመጡ ቱሪስቶችን፣ የንግዱን ማኅበረሰብ እና ባለሀብቶችን ቁጥር እንደሚያሳድግና በተዘዋዋሪም ለሩሲያ ተመሳሳይ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ታንዛኒያ “የሁለቱ አገራት የጋራ ሥራ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ መሻሻል እንዲያሳይ የማድረግ ጥረቷን” ትቀጥላለች ብለዋል።

በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በቱሪዝም ዘርፎች ስላለው የሩሲያ-ታንዛኒያ አጋርነት የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0