የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ

ቦርዱ፣ የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት እና የቆጠራና ውጤት የማሳወቅ ቀሪ ሥራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ በድምጽ መስጫ ሂደትን ተከትሎ በተፈጠረው ሰልፍ የድምጽ መስጫ ጊዜ በመራዘሙ ምክንያት በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ አማራ፣ ሶማሌ ክልሎች እና በአዲስ አበባ የድምጽ ቆጠራ አለመጠናቀቁን መናገራቸውን መግለጫውን የተከታተለው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

የቦርዱ ሰብሳቢ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦቹ፦

የ የድምፅ መስጫ ሠዓት መራዘሙና የቴክኒክ ፈተናዎች ለቆጠራው መዘግየት ምክንያት ሆነዋል፡፡

በአዲስ አበባ አንድ ሺህ ጣቢያዎች ላይ ቆጠራው ገና አልተጠናቀቀም።

የሳጥኖች መሙላትና የወረቀቶች መተለቅ ፈተና ነበሩ።

በአሁኑ ወቅት የድምፅ ማዳመር ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ቦርዱ የተለያዩ ቅሬታዎች በተለያየ መንገድ አስተናግዷል፡፡

ቅሬታዎችን ለማጣራት፣ ለማረጋገጥ እና ማስረጃ የማጠናቀር እየሠራ ይገኛል።

ያልተገባ ተግባር የፈጸሙ ሁለት ሠራተኞች ከሥራ ተሰናብተዋል።

በተለያዩ ቦታዎች የምርጫ ውጤት በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ተደምሮ ያለቁት ለሕዝብ ይፋ ሆነዋል፡፡

በቀጣይ ውጤቱን ለማረጋገጥና ይፋ ለማድረግ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት እንዲመጣ ይደረጋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0