ሩቶ የትችት ማዕበል ያስከተለውና በአሜሪካ የሚደገፈው የኢቦላ ማዕከል ግንባታን ተከላከሉ - መገናኛ ብዙኃን

ሰብስክራይብ

ሩቶ የትችት ማዕበል ያስከተለውና በአሜሪካ የሚደገፈው የኢቦላ ማዕከል ግንባታን ተከላከሉ - መገናኛ ብዙኃን

የኬንያው ፕሬዝዳንት ማዕከሉን ለመገንባት የፈቀዱት በአሜሪካ ጥያቄ መሠረት መሆኑንና ይህም በኮቪድ-19 ወቅት በነበረው የረጅም ጊዜ የጤና ትብብር ላይ የተመሠረተ መሆኑን አንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ኬንያውያንንም ሆነ የውጭ አገር አጋሮችን ሊያጋጥሙ ለሚችሉ የኢቦላ ጉዳዮች ኬንያ ዝግጁ መሆን አለባት ሲሉ መከራከሪያቸውን ማቅረባቸውን ዘገባው አክሎ ገልጿል።

“እኛ ኃላፊነት የሚሰማን መንግሥት ነን። ምን እያደረግን እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን” ብለዋል።

በማዕከላዊ ኬንያ በሚገኝ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ ላይ ለአሜሪካ ዜጎች ለይቶ ማቆያ (ኳራንቲን) ሥፍራ የሚፈጥረው ይህ ዕቅድ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ የመጣ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ተገልጿል። ባለፈው ሰኞ የናኑኪ ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት ሊከሰት የሚችለውን የኢቦላ አደጋ በማስጠንቀቅ እና ኬንያ ለምን ለአሜሪካውያን የሚሆን ማዕከል እንደምታስተናግድ በመጠየቅ ሰላማዊ ተቃውሞ አድርገዋል።

እንደ መገናኛ ብዙኃኑ ዘገባ፣ ፕሮጀክቱን ለማስቆም ሕጋዊ የክስ ሂደት የተጀመረ ሲሆን፣ ፍርድ ቤትም ከሕዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ዕቅዱን በጊዜያዊነት አግዶታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0