የሩሲያ ፌደራል የደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ኢላማ ያደረገ የውጭ አገር የስለላ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር ዘመቻን አከሸፈ
16:54 02.06.2026 (የተሻሻለ: 17:04 02.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ፌደራል የደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ኢላማ ያደረገ የውጭ አገር የስለላ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር ዘመቻን አከሸፈ
የሩሲያ የፌደራል የደኅንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ፤ የከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣናትን ስማርት ስልኮች ለመበርበር ተንኮል-አዘል ሶፍትዌሮችን የተጠቀመ የውጭ አገር የስለላ ዘመቻ መጋለጡን አስታውቋል።
ይህ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር የተቀረጸው የሚከተሉትን ድርጊቶች ለመፈጸም ነበር፦
▪ መረጃዎችን ለመመንተፍ (ለመውሰድ)፤
▪ ንግግሮችን በስውር ለማዳመጥ፤
▪ ያለማንም እውቅና ሁኔታዎችን በምስጢር ለመሰለል።
የፌደራል የደኅንነት አገልግሎቱ በኮምፒውተር መረጃዎች ላይ ሕገ-ወጥ መግባት በመፈጸም እና ተንኮል-አዘል ሶፍትዌሮችን በማሰራጨት ወንጀል ክስ መስርቶ ምርመራ ጀምሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X