የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በፑቲን ግብዣ የመጀመሪያ ይፋዊ መንግሥታዊ ጉብኝት በሩሲያ ሊያደርጉ ነው
14:04 02.06.2026 (የተሻሻለ: 14:24 02.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በፑቲን ግብዣ የመጀመሪያ ይፋዊ መንግሥታዊ ጉብኝት በሩሲያ ሊያደርጉ ነው
ፕሬዝዳንቷ ከረቡዕ እስከ ዓርብ በሩሲያ ይፋዊ የመንግሥት ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፤ ይህም ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ግንኙነት እንደሚሆን የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ይህ ጉብኝት እ.አ.አ በ1969 ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ ወደ ሞስኮ ካደረጉት ጉዞ በኋላ፣ አንድ የታንዛኒያ የመንግሥት መሪ ወደ ሩሲያ ያደረገው የመጀመሪያው ታሪካዊ ጉብኝት ነው።
ታሪካዊ ጉብኝቱ የሚከተሉትን ያክትታል፦
🟠 በክሬምሊን የሚደረጉ ውይይቶች፣
🟠በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ መሳተፍ እና
🟠 በታንዛኒያ–ሩሲያ የቢዝነስ ፎረም ላይ የሚደረግ ንግግር።
ውይይቶቹ በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኩራሉ ተብሎ ይጠበቃል፦
🟠 በንግድ፣
🟠 በኢነርጂ፣
🟠 በትምህርት እና
🟠 በመሠረተ ልማት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X