በዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ላይ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን ተሳትፎ 80% ለማድረስ ታቅዷል - የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
13:32 02.06.2026 (የተሻሻለ: 13:34 02.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ላይ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን ተሳትፎ 80% ለማድረስ ታቅዷል - የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
በአሁኑ ወቅት ፈቃድ ካላቸው የሀገር ውስጥ ተቋራጮችና አማካሪዎች መካከል በዓለም አቀፍ ጨረታዎች ላይ ለመወዳደር የሚያስችል የቴክኒክና የክንውን አቅም ያላቸው 33 በመቶ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን በዘንድሮው በጀት ዓመት የተካሄደ ጥናት አመላክቷል፡፡
ይህንን አሃዝ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ 55 በመቶ ከዚያም በዓሥር ዓመቱ እቅድ ወደ 80 በመቶ ለማሳደግ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ኩባንያዎችን ተወዳዳሪነት የሚገድቡ ማነቆዎችን ለመፍታት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
እቅዱ የኢትዮጵያን የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ከሀገር ውስጥ ገበያ ባለፈ እያደገ የመጣው የቀጣናዊ መሠረተ ልማት ፍላጎት ባለባቸው የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሄደው እንዲወዳደሩ ለማዘጋጀት ያለመ መሆኑ ተዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X