በምርጫ ጣቢያዎች ሰልፍ ላይ ያሉ መራጮች ድምፅ ሰጥተው እስኪጨርሱ ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ይቀጥላል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
19:04 01.06.2026 (የተሻሻለ: 19:34 01.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በምርጫ ጣቢያዎች ሰልፍ ላይ ያሉ መራጮች ድምፅ ሰጥተው እስኪጨርሱ ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ይቀጥላል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየው የ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላልተወሰኑ ሰዓታት መራዘሙን አስታውቋል።
ድምፅ አሰጣጡ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ ባይጠናቀቅም፤ እስከዚያው ሰዓት ድረስ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ሰልፍ ላይ የነበሩ መራጮች በሙሉ፣ ድምፅ ሰጥተው እስኪጨርሱ ሂደቱ እስከ እኩለ ሌሊት 6፡00 ሠዓት የሚቀጥል መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።
በሰልፍ ላይ የሚገኙ ዜጎች በሙሉ የመምረጥ መብታቸው ተከብሮ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ለማስቻል በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓትን ማራዘም በሚፈቅደው በምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) ላይ በተደነገገው መሠረት ውሳኔውን ማሳለፉን ቦርዱ አመላክቷል።
በስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረቦች የተቀረጸ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X