"በምርጫ ቦርድ እና እስካሁን ባሳዩት ሙያዊ ብቃት እጅግ ተገርመናል" – የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን መሪ

ሰብስክራይብ

"በምርጫ ቦርድ እና እስካሁን ባሳዩት ሙያዊ ብቃት እጅግ ተገርመናል" – የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን መሪ

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ እስካሁን ባለው ሂደት መደሰታቸውን ገልጸዋል።

“እስካሁን ድረስ፣ በአጠቃላይ እኛ ጉብኝት ባደረንባቸው ቦታዎች የምርጫው ሰላማዊ ባህሪ በጣም ደስተኞች ነን። ህዝቡ ታጋሽ ሆኖ፣ ተሰልፎ፣ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም እየተጠባበቀ ነው። በድጋሚ ላሰምርበት የምፈልገው፣ በምርጫ ቦርድ እና እስካሁን ባሳዩት ሙያዊ ብቃት እጅግ መገረማችንን ነው። እኛ በነበርንባቸው ቦታዎች የነበረው የፀጥታ ሁኔታም እንዲሁ ጥሩና የተረጋጋ ነበር።” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠራተኞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያውቁ ይመስላል ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ሁሉም ነገር የተስተካከለና ስርዓትን የተከተለ እንደሚመስል ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን ከተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የተገኙ የታዛቢነት መረጃዎች በሙሉ ተጠናቅቀው ሲሰበሰቡ፣ ሙሉ እና አጠቃላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0