የፓን-አፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር አኅጉራዊ የሕክምና እንክብካቤን ለማጠናከር ያለመ የመመሥረቻ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሄደ
17:14 01.06.2026 (የተሻሻለ: 17:24 01.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የፓን-አፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር አኅጉራዊ የሕክምና እንክብካቤን ለማጠናከር ያለመ የመመሥረቻ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሄደ
ማኅበሩ በአፍሪካ የኤችአይቪ እንክብካቤና ሕክምናን ለማሻሻል የሕክምና ባለሙያዎችንና አጋሮችን ያስተባበረ ታላቅ ጉባኤ በአዲስ አበባ ማካሄዱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ማኅበሩ የአፍሪካ ክሊኒሻኖችን አንድ ላይ ለማስተባበርና አብሮ ለመሥራት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
"የማኅበሩ መመሥረት ሀገራት ክሊኒካዊ የትግበራ ሳይንስና ምርምሮችን እንዲጋሩ በር ይከፍታል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኗንና በተለይም ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍን መግታት ላይ ትኩረት እንደምታደርግ አስታውቀዋል።
የማኅበሩ ሊቀመንበር ዶ/ር ሙሃንግዊ ሙላውዲ በበኩላቸው ማኅበሩ በአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መመሥረቱ የአፍሪካውያን አንድነት ማሳያ መሆኑንና በዘርፉ የሚሠሩ ባለሙያዎችን ድምፅ ለማሰማትና አብሮነትን ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X