"ምርጫውን የሚያሸንፈው ፓርቲ የኑሮ ውድነትን የማሻሻልና ሰላምን የማስፈን ግዴታ አለበት" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ
15:55 01.06.2026 (የተሻሻለ: 16:04 01.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"ምርጫውን የሚያሸንፈው ፓርቲ የኑሮ ውድነትን የማሻሻልና ሰላምን የማስፈን ግዴታ አለበት" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ
“በ5 ዓመት አንዴ የማገኘውን መብት ዝም ብዬ አሳልፌ አልሰጥም” ያሉት ካፒቴን ዘሪሁን መለሰ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ሁሉም ሀገር አቀፍ ምርጫዎች መሳተፋቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"የሚያስተዳድረኝ ተመርጦ አሸናፊ የሚሆነው ፓርቲ ትልቅ ኃላፊነት እየሰጠነው ነው፡፡ ... ይሄ ሁሉ ሰው (መራጩ ሕዝብ) ለውጥ ይፈልጋል፡፡ ይሄንን ለውጥ ማምጣት ግዴታው ይሆናል፡፡" ብለዋል፡፡
የምርጫ ክልል 28 (የካ ክፍለ ከተማ) የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ባደረገው ቅኝት የተስተዋሉ ዋና ዋና ነጥቦች፦
አረጋውያን፣ እናቶች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ልዩ ተልዕኮ ያለባቸው (የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች) ቅድሚያ እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።
ምርጫው በአብዛኛው አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ የቀጠለ ሲሆን፣ መራጮችም ሂደቱ እንዲፈጥን እየጠየቁ ይገኛሉ።
በምስራቅ ጮራ 02፣ ብሎኬት ቀጣና፣ ቦሌ ጀሊሲ፣ ፔፕሲ ሜዳ እና ዕድር ሜዳ ጣቢያዎች መራጮች በረጅም ሰልፍ ተራቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ።
የምርጫ ጣቢያዎቹ አስተባባሪዎችና ታዛቢዎች በየጣቢያዎቹ በወቅቱ ተገኝተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia