ማዳጋስካር ከሩሲያ ጋር ያላትን የወታደራዊ ግንኙነት ለደኅንነቷ እና ለሰላሟ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ማዳጋስካር ከሩሲያ ጋር ያላትን የወታደራዊ ግንኙነት ለደኅንነቷ እና ለሰላሟ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን አስታወቀች

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፤ በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የማዳጋስካር ወታደራዊ ትጥቅ እና መሣሪያዎች የሩሲያ ምርቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

▫ ሩሲያ እና ማዳጋስካር በቅርቡ ወታደራዊ ትብብራቸውን በማጠናከር የሩሲያ የአፍሪካ ኮርፕስ አሰልጣኞች ለ127 ለተመረጡ የማዳጋስካር ልዩ ኃይል አባላት ለ8 ሳምንታት የዘለቀ ሥልጠና የሰጡ ሲሆን፣ መሠረታዊ የድሮን አጠቃቀም እና የተኩስ ልምምድ ሥልጠናዎችንም አካትተዋል።

በተጨማሪም ሩሲያ ሁለት የ‘ቢኤምፒ-3’ ዘመናዊ የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን (የጦር መኪኖችን)፣ የጦር መሣሪያ ጥይቶችን እና አነስተኛ የጦር መሣሪያዎችን ለሀገሪቱ በዕርዳታ አበርክታለች።

ቪዲዮው የየብስ ላይ የውጊያ ተሽከርካሪን፣ የታንክ አጥፊነትን እና በውኃ ላይ የመንሳፈፍ ብቃትን በአንድ ላይ ያቀፈውን ሁለገብ ‘ቢኤምፒ-3’ የታጠቀ የጦር መኪና የሙከራ እሽቅድድም ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0