"ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል" - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

© telegram sputnik_ethiopia"ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል" - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.06.2026
ሰብስክራይብ

"ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል" - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ የፈረንሳይ ጉራራ ነዋሪ የሆኑት ይልማ ሲደልል ይበጀኛል የሚሉትን መሪ ለመምረጥ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ተሰልፈው ሲጠባበቁ እንደነበር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“ምርጫ ማለት ለእኛ እና ለሀገራችን የሚበጅ፤ ለህዝባችን የሚበጅ ሰው የምንመርጥበት ነው። በትክክል ሰርቶ ህዝቡን የሚመራ ሰው እንፈልጋለን። ለዚህ ነው በሌሊት መጥቼ የተሰለፍኩት፡፡” ብለዋል፡፡

የፈረንሳይ ጉራራ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ፀጋዬ ረጋሳ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደምም የምርጫ ልምድ እና ግንዛቤ እንደነበራቸው በመግለጽ፣ ሀገሪቷንም ህዝቡንም ይመራል ብለው የሚገምቱትን ዕጩ ተወዳዳሪ እንደመረጡ ተናግረዋል፡፡

"... እኔ አሁን ለምሳሌ ለራሴ የሚያስፈልገኝን ጥሩ ሰው ወይም ደግሞ ሀገሬን ይመራል ህዝብን ያስተዳድራል ብዬ ያመንኩበትን አሁን መርጬ ነው የወጣሁት።” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia"ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል" - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
ምርጫው ይበጀናል ያልነውን መሪ የመረጥንበት እድል ሰጥቶናል - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.06.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0