በኢትዮጵያ ድምፅ አሰጣጥ በጥሩ ሁኔታ ተጀምሯል፤ ሂደቱ በስኬት እንደሚቀጥል ፅኑ እምነት አለን - የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ
በኢትዮጵያ ድምፅ አሰጣጥ በጥሩ ሁኔታ ተጀምሯል፤ ሂደቱ በስኬት እንደሚቀጥል ፅኑ እምነት አለን - የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ልዑካቸው በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በመታዘብ ላይ ይገኛሉ።
በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው የድምፅ አሰጣጥ መክፈቻ ሂደቶችንና የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝግጁነት የተመለከቱት ኡሁሩ ኬንያታ፤ እስካሁን ባለው ምልከታ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ምርጫው የሕዝብን እውነተኛ ውክልናና፣ ፍላጎት ማካተትን በማረጋገጥ በአፍሪካ አኅጉር ዴሞክራሲን ለመገንባት ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በዶ/ር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የታዛቢዎች ቡድንም የጠዋቱን የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በመከታተል ላይ ናቸው።
ሁለቱም አኅጉራዊና ቀጣናዊ ታዛቢ ቡድኖች በምርጫ ጣቢያዎች የታየውን ሰላማዊ ከባቢና የሴት መራጮችን ከፍተኛ ተሳትፎ አድንቀው፣ ሙሉ የዕለቱን የድምፅ አሰጣጥና የቆጠራ ሂደት ታዝበው የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ቅኝት ሲያደርጉ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X