በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከጠቅላላው መራጭ ውስጥ 49.3%፣ ከዕጩዎች መካከል ደግሞ 26% ሴቶች ናቸው - የኢትዮጵያ ሴቶች ኮንፌዴሬሽን
12:05 01.06.2026 (የተሻሻለ: 12:14 01.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከጠቅላላው መራጭ ውስጥ 49.3%፣ ከዕጩዎች መካከል ደግሞ 26% ሴቶች ናቸው - የኢትዮጵያ ሴቶች ኮንፌዴሬሽን
ኮንፌዴሬሽኑ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተመዘገቡት 54 ሚሊዮን 057 ሺህ 861 መራጮች መካከል 26 ሚሊዮን 667 ሺህ 132ቱ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቋል።
የኮንፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገነት ሥዩም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሴቶች በዕጩነትም ጭምር ሰፊ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑንና ከጠቅላላው ተወዳዳሪዎች መካከል 25.8 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
የሴት ዕጩዎች ውክልና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በተለይም የሞጆ ከተማ የ71.4 በመቶ ከፍተኛ የሴት ዕጩዎች ድርሻ ያስመዘገበ ሲሆን በአርሲ፣ ኢሉባቦር፣ አማራ እና ጋሞ ዞኖችም ጠንካራ የሴቶች ዕጩነት መታየቱ ተገልጿል።
በስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረቦች የተቀረጸ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X