"የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን ዕድል ለመወሰን መካሪና ገሣጭ እንደማይሻ በተግባር አሳይቷል" – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰብስክራይብ

"የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን ዕድል ለመወሰን መካሪና ገሣጭ እንደማይሻ በተግባር አሳይቷል" – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ዐቢይ አሕመድ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዕጩ ተወዳዳሪነት በቀረቡበት በጅማ ዞን የጎማ 2 ምርጫ ክልል፣በበሻሻ የድምጽ ጣቢያ ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ “የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች” "ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም የሚል እምነት እንዲያዝ” የሚገዟቸውን ኃይሎች ገዝተው በስፋት ማሰማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከማለዳው ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምልከታቸው ማረጋገጣቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

“ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት፣ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመገንባት የሚሻውን፣ የሚፈልገውን ለመወሰን መካሪና ገሣጭ እንደማያስፈልገው ያሳየበት እርምጃ ነው።" ሲሉ አክለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0