ባለ ከፍተኛ ማዕረጓ ቤኒናዊት መኮንን የመጀመሪያዋ ሴት የፕሬዚዳንቱ ረዳት በመሆን አዲስ ታሪክ ሠራች

ሰብስክራይብ

ባለ ከፍተኛ ማዕረጓ ቤኒናዊት መኮንን የመጀመሪያዋ ሴት የፕሬዚዳንቱ ረዳት በመሆን አዲስ ታሪክ ሠራች

ካፒቴን ኤልቪር ቱፔ በአዲሱ የሀገሪቱ መሪ ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ለዚህ የኃላፊነት ቦታ መሾሟን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ቶፎ ከሚገኘው ብሔራዊ የመኮንኖች ትምህርት ቤት የተመረቀችው ካፒቴን ኤልቪር፤ በቤኒን የምድር ጦር ከፍተኛውን ማዕረግ የያዘች ሴት ሆናለች።

ካፒቴን ቱፔ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ፤ “የፕሬዚዳንቱ ረዳት እንደመሆን ሚናዬ እሳቸውን ማገዝ እና በሥራ እንቅስቃሴዎቻቸው እንዲሁም በጉዞዎቻቸው ወቅት በዙሪያቸው ያሉትን ሁሉንም የደኅንነት ጥንቃቄዎች ማስተባበር ነው” ብላለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaባለ ከፍተኛ ማዕረጓ ቤኒናዊት መኮንን የመጀመሪያዋ ሴት የፕሬዚዳንቱ ረዳት በመሆን አዲስ ታሪክ ሠራች
ባለ ከፍተኛ ማዕረጓ ቤኒናዊት መኮንን የመጀመሪያዋ ሴት የፕሬዚዳንቱ ረዳት በመሆን አዲስ ታሪክ ሠራች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.05.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0