ይህ የተገለፀው ዓለም አቀፉን የሰላም አስከባሪዎች ቀን በማስመልከት በተዘጋጀ መርኃ-ግብር ላይ ነወ።
19:31 30.05.2026 (የተሻሻለ: 19:44 30.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን የምታከናውነው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለሀገሪቱ መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለፀ
ይህ የተገለፀው ዓለም አቀፉን የሰላም አስከባሪዎች ቀን በማስመልከት በተዘጋጀ መርኃ-ግብር ላይ ነወ።
የደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አልቢኖ አኮል አታክ፤ "ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራትን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ የምትጫወተው ሚና በቀጣናው መልካም ዝምድና እንዲጠናከር የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል" ብለዋል።
🪖 ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ሕዝብን መሠረት አድርጎ የሚያከናውናቸውን የሰብዓዊ መብት ተልዕኮዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የ21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በሴክተር ሳውዝ ጁባ እና በዌስተርን ኢኳቶሪያ ሰፊ ቀጣናን በመሸፈን የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia