የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

© telegram sputnik_ethiopiaየድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.05.2026
ሰብስክራይብ

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

4 ሺህ ሄክታር የመስፋት አቅም ያለውን የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና፤ ከአማራጭ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶች ጋር ማስተሳሰር ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሬት እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጸጋዬ ዘካሪያስ በባቡር ፕሮጀክቱ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በተደረገበት መድረክ ላይ ገልጸዋል።

 

በአሁኑ ወቅት ወደ ነፃ ንግድ ቀጣናው የሚገቡና የሚወጡ ጭነቶች በአብዛኛው በመኪና የሚጓጓዙ በመሆኑ ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እያስወጣ እንደሆነ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።

የባቡር መስመር ፕሮጀክቱ እውን ሲሆን 30 በመቶ ያህሉን የጭነት ማጓጓዣ ከጎዳና ወደ ባቡር ለማሸጋገር መታቀዱንና የፕሮጀክቱ የጥናት ሥራዎች ተጠናቀው ለኢንቨስትመንት ዝግጁ እንደሆኑም ታክሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0