ለጋሾች ቃላቸውን በማጠፋቸው የኢቦላ መከላከያ የገንዘብ ድጋፍ በግማሽ ገደማ መቀነሱን የአፍሪካ ሲዲሲ አስታወቀ
17:14 30.05.2026 (የተሻሻለ: 18:55 30.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለጋሾች ቃላቸውን በማጠፋቸው የኢቦላ መከላከያ የገንዘብ ድጋፍ በግማሽ ገደማ መቀነሱን የአፍሪካ ሲዲሲ አስታወቀ
ሰኞ ዕለት ለኢቦላ ወረርሽኝ ቁጥጥር ቃል የተገባው 500 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የገንዘብ ድጋፍ፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ 290 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ገልጸዋል።
አንዳንድ ለጋሾች የገቡትን ቃል “ስህተት ነበር” ማለታቸውን በመጥቀስ የተሰማቸውን ቅሬታ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ “ሰዎች እየሞቱ፤ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” ሲሉ ጠይቀዋል።
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኡጋንዳ የተከሰተው የቦንዲቡግዮ ዝርያ በኮንጎ 1,077 ሰዎችን እንዳጠቃ እና 246 የሚሆኑትን እንደቀጠፈ የተጠረጠረ ሲሆን በኡጋንዳ ደግሞ 8 ሰዎችን እንደያዘ ተረጋግጧል።
ዶክተር ካሴያ ለዓለም ባንክ እና ለአፍሪካ ልማት ባንክ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ አሜሪካ ከኮንጎ፣ ከኡጋንዳ እና ምንም ዓይነት ኢቦላ ካልተመዘገበባት ደቡብ ሱዳን ጭምር በሚመጡ መንገደኞች ላይ የጣለችውን አዲስ የጉዞ ገደብ ተችተዋል።
አክለውም “ይህንን ወረርሽኝ ያለ በቂ ምንጭ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ምዕራባውያን በአፍሪካ ሀገራት ላይ በሚጥሉት የጉዞ ገደብ ማቆም አንችልም” ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X