‘ተጎጂዋ አፍሪካ ናት’፤ ፈረንሳይ የባሪያ አገዛዝ ሕጓን መሰረዟን ተከትሎ ካሳ የመጠየቂያው ጊዜ አሁን ነው - የኒጀር ባለሙያ
17:19 30.05.2026 (የተሻሻለ: 17:24 30.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
‘ተጎጂዋ አፍሪካ ናት’፤ ፈረንሳይ የባሪያ አገዛዝ ሕጓን መሰረዟን ተከትሎ ካሳ የመጠየቂያው ጊዜ አሁን ነው - የኒጀር ባለሙያ
የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ‘ኮድ ኑዋር’ የተሰኘውን የባሪያ አገዛዝ ሕግ ለመሰረዝ ድምፅ መስጠታቸው ስለ ካሳ ክፍያ ጥብቅ ውይይቶችን ለማድረግ መንገድ ሊከፍት ይገባል ሲሉ የዩናይትድ ኒጀር ፌዴሬሽን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ሳሊፉ ባኮ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የባሪያ ንግድ እና የባርነት ታሪክ በድጋሚ ሊመረመር ይገባል፤ ነገር ግን ይህ ኃላፊነት ከምንም በላይ የአፍሪካ መሪዎች ትከሻ ላይ የሚወድቅ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
“ግልጽ እና የተሟላ ምርመራ በማድረግ፤ በባርነት ምክንያት እነማን እና ምን ምን ነገሮች ተጎጂ እንደሆኑ መለየት የሚችሉት የአፍሪካ መሪዎች ብቻ ናቸው።”
የአፍሪካ ሀገራት ይህንን የፈረንሳይ ውሳኔ በመጠቀም ካሳ ሊጠይቁ ይገባል ሲሉም አክለዋል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት በፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ውስጥ የባርነት ሥርዓት የሚደነግገውን የ17ኛ ክፍለ ዘመን ‘ኮድ ኑዋር’ (የጥቁሮች ሕግ) አዋጅ ለመሰረዝ በሙሉ ድምፅ ወስኗል። የባርነት ሥርዓት እ.አ.አ በ1848 ቢሻርም፤ ሕጉ ግን እስካሁን በይፋ ሳይሰረዝ ቆይቷል። የሕጉ መሻር ፈረንሳይ እ.ኤ.አ በ2001 የባሪያ ንግድ እና ባርነትን በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች አድርጋ ከፈረጀችበት ውሳኔ ጋር የሚጣጣም ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X