ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
14:51 30.05.2026 (የተሻሻለ: 14:54 30.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰኞው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 057 ሺህ 871 መራጮች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ መቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል።
ቦርዱ የምርጫ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ማድረሱን፣ የዜጎችን ግንዛቤ ለማሳደግ በ5 ቋንቋዎች 19 የሕዝብ ክርክሮችን ማደራጀቱንና ከ250 ሺህ በላይ የታዛቢዎች ባጅ ማሰራጨቱን ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።
ምርጫውን የአፍሪካ ኅብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይታዘባሉ።
በምርጫ ቦርድ የግዜ ሠለዳ መሠረት የድምጽ ውጤት ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X