‘ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ትብብር እና ቀጣናዊ የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥ ማሳደግ አለብን’ - የናይጄሪያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

‘ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ትብብር እና ቀጣናዊ የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥ ማሳደግ አለብን’ - የናይጄሪያዊ ባለሙያ

“ምንም እንኳን 20 የአፍሪካ ሀገራት ከ5 በመቶ በላይ ዕድገት እያስመዘገቡ ቢሆንም፤ ሁሉንም ሀገራት ግምት ውስጥ ስናስገባ ግን የዕድገት ትንበያው በአማካይ ከ4.4 በመቶ ወደ 4.2 በመቶ ዝቅ ይላል [...] ይህም ከታቀደው የ7 በመቶ ዕድገት እጅግ የራቀ ነው” ሲሉ የልማት ኢኮኖሚ ባለሙያው ኬን ኢፌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

እንደ ኬን ኢፌ ገለጻ፤ ዋና ዋናዎቹ ፈተናዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠 እየተባባሰ የመጣው የሥራ አጥነት እና የድህነት ደረጃ፣

🟠 የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የነዳጅ፣ የማዳበሪያ እና የትራንስፖርት ወጪዎችን በመስቀል የምግብ ዋጋ ግሽበት እንዲንር ማድረጉ፣

🟠 25 የሚጠጉ የአፍሪካ ሀገራት የገጠማቸው የገንዘብ ዋጋ ማሽቆልቆል፤ የግሽበት መጨመር እና ሀገራዊ ዕዳ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ።

ይሁን እንጂ “በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሀገር ውስጥ ገቢያቸውን ሊያሳድጉ የሚችሉ ማሻሻያዎችን እያደረጉ ነው” ሲሉም አክለዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ደረጃቸውን እንዴት እያሻሻሉ እንደሚገኙ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በመበደር ረገድ የገጠሟቸውን ፈተናዎች ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0