የአፍሪካ ሴቶች አቅም 'በቂ ዋጋ አይሰጠውም' - የሴት መሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች
09:26 30.05.2026 (የተሻሻለ: 09:34 30.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሴቶች አቅም 'በቂ ዋጋ አይሰጠውም' - የሴት መሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች
የካሜሮኗ ከተማ ዱዋላ የሴቶች መሪነትን የማሳደግ ዓላማ ያነገበውን የኤፍ-ዩኒየን የአፍሪካ ጉባዔ 2026 እያስተናገደች ትገኛለች።
በርካታ ተሳታፊዎች በንግድ እና በአመራር ዓለም ላሉ የአፍሪካ ሴቶች የበለጠ እይታ፣ የተሻለ እውቅና እና ጠንካራ ድጋፍ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት አፅንዖት ሰጥተዋል።
"ዛሬ ሴቶች ፈጣሪ ናቸው። ዕድሎችን ማግኘት ይችላሉ? በቂ የፋይናንስ አቅርቦት አላቸው? የነገ መሪዎች እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን ትስስሮች በበቂው ማግኘት ይችላሉ?" ሲሉ የጉባዔው መሥራች ኡርሱል ዎንጄ ጠይቀዋል።
ሴቶች ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የጥርጣሬ እና ትችታዊ ዕይታ ይገጥማቸዋል የሚሉት ደግሞ የጉባዔው ተሳታፊ እና የድርጅት ኃላፊ ቲማ ሴባሂ ናቸው።
ሆኖም ሴቶች ለውሳኔ አሰጣጥ የተለየ እና ብዙ ጊዜ በጣም ውጤታማ መንገዶችን ይፈጥራሉ ሲሉ በዱዋላ ራስ ገዝ ወደብ የእንጨት ተርሚናል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሶላንጅ ፍሎሬ ኢያንጎ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X