የአንድ ወገን ማዕቀብ ዓለም አቀፍ ሕግ እና የተመድ ቻርተርን በመጣስ የዓለም የንግድ ሥርዓትን እያናጋ ነው - ኢትዮጵያዊ የሕግ ባለሙያ
08:03 30.05.2026 (የተሻሻለ: 08:04 30.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአንድ ወገን ማዕቀብ ዓለም አቀፍ ሕግ እና የተመድ ቻርተርን በመጣስ የዓለም የንግድ ሥርዓትን እያናጋ ነው - ኢትዮጵያዊ የሕግ ባለሙያ
አንዳንድ ሀገራት ሌላውን ለመጉዳት እንዲሁም ተፎካካሪያቸውን ለማዳከም ከብሔራዊ ጥቅማቸው ጋር እያያዙ የሚጥሉት ማዕቀብ ከአግባብ ወጪ እንደሆነ የሕግ ባለሙያ እና ተመራማሪ መታገስ ውለታው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
"ማዕቀብ ባልተገባ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሲውል እያየን ነው። ይህ ደግሞ የዓለም የንግድ ድርጅት ዓላማውን እንዳያሳካ፣ የዓለም የንግድ ሕግጋት ተግባራዊ እንዳይሆኑ እንዲሁም የዓለም የንግድ ስርዓት እንዲፋለስ የማድረግ ውጤት እንዳለው ይታያል።"
በውጭ ሀገራት የተቀመጡ ሉዓላዊ ሀብቶችን ይዞ መውረስ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ባለሙያው ጨምረው ገልጸዋል።
ለዚህም ኢራን እና ሩሲያ በምዕራባውያን የዘፈቀደ እርምጃ የደረሰባቸውን የሀብት እገታ በማንሳት፤ እንደዚህ ዓይነት የአንድ ወገን እርምጃዎች ከባድ መዘዝ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
"ሕጉ እየተጣሰ ሁሉም በጉልበቱ መመራት ከጀመረ፤ የዓለም የንግድ ስርዓት፣ የዓለም ኢንቨስትመንት በሙሉ እንዲዳከም ነው የሚያደርገው። ወደ ጦርነትም ሊወስድ ይችላል። የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ወደ ሌላ የዓለም ጦርነት ሊያመሩ ይችላሉ።"
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም ከሱዳን አቻቸው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ ሕገ-ወጥ ማዕቀቦች የዓለም አቀፋዊነት መርሆችን እንደሚጥሱ የሚገልፁበት ቪዲዮ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X