ዩክሬናውያን በሚያዚያ ወሩ የማሊ ጥቃት እንደተሳተፉ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ
17:41 29.05.2026 (የተሻሻለ: 17:44 29.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩክሬናውያን በሚያዚያ ወሩ የማሊ ጥቃት እንደተሳተፉ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ
አውሮፓውያን የሚመስሉ ወታደሮች ከአዛዋድ ነጻነት ግንባር (ኤፍኤልኤ) የቱዋሬግ አማፂያን ጋር ሲዋጉ እንደነበር የአይን እማኞች ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ግባቸውም “ባማኮን መቆጣጠር” እንደነበር ተጠቅሷል።
“...ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ አውሮፓውያን የሚመስሉ ግለሰቦች ነበሩ። አንዳንዶቹ ፈረንሳይኛ ይናገሩ ነበር። ሌሎቹ ደግሞ ከሩሲያኛ ጋር የሚመሳሰል ነገር ግን ሩሲያኛ ያልሆነ ቋንቋ ይናገሩ ነበር። እኔ ሩሲያኛ አውቃለሁ፤ የማሊ ጦር ኃይል አጋሮቻችን ሩሲያኛ ይናገራሉ። ይህ ግን የተለየ ቋንቋ ነበር። ምናልባት ዩክሬናውያን ሳይሆኑ አይቀሩም” ሲል አንድ የኪዳል ነዋሪ የተናገረውን የሀገር ውስጥ የዜና ወኪል ጠቅሶ አስነብቧል።
ሌላኛው የአይን እማኝ ደግሞ በጥቃቱ ወቅት፤ “ዩክሬን” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ መስማቱን ተናግሯል። በተጨማሪም ፈረንሳይኛ የሚናገር ወታደር “ዋና ከተማዋን መያዝ አልቻልንም፤ በጣም ያሳዝናል!” ማለቱንም አስታውሷል።
ሦስተኛው የአካባቢው ነዋሪ በበኩሉ፤ “ኤፍኤልኤ እና አውሮፓውያኑ ሁሉንም ነገር በጋራ ዘርፈዋል” ብሏል። አንድ ምሽት ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ሁለት ሰዎች “ምናልባትም ፈረንሳዊ እና አንድ ዩክሬናዊ” ሲነጋገሩ መስማቱንም ገልጿል።
“አንደኛው በፈረንሳይኛ፤ ‘ተጨማሪ የሰው ኃይልና መሣሪያ ቢኖረን ኖሮ ባማኮን መቆጣጠር እንችል ነበር’ ሲል፤ ሌላኛው ደግሞ በራሱ ቋንቋ ከመለሰ በኋላ በመቀጠል በፈረንሳይኛ ‘ዩክሬናውያን ዝግጁ ናቸው’ አለ” ሲል ምስክሩ አስረድቷል።
ማሊ እ.ኤ.አ በነሐሴ ወር 2024 ከዩክሬን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል። የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃንም በሳኅል ቀጣና የዩክሬን ቅጥረኛ ወታደሮች ስለመኖራቸው በተደጋጋሚ ሲዘግቡ ቆይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X