ኬንያ በኢቦላ ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ሀገር መቆጠር የለባትም - ባለሥልጣን
16:59 29.05.2026 (የተሻሻለ: 17:40 29.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኬንያ በኢቦላ ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ሀገር መቆጠር የለባትም - ባለሥልጣን
ሁሉም የኢቦላ ታማሚዎች እና በበሽታው የተጠቁ ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ የተሻለ እንክብካቤ ማግኘት ይገባቸዋል ሲሉ የኬንያ የሕግ ማኅበር ፕሬዝዳንት ቻርለስ ካንጃማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
አስተያየታቸው፤ ማርኮ ሩቢዮ የኢቦላ ታማሚዎች ወደ አሜሪካ እንደማይገቡ መግለጻቸውን ተከትሎ፤ የትራምፕ አስተዳደር ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኡጋንዳ የወረርሽኝ ቀጣናዎች ለሚወጡ አሜሪካውያን፤ ኬንያ ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ መር የኢቦላ ሕክምና ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደ የሚጠቁሙ ዘገባዎች ከወጡ በኋላ የመጣ ነው።
“ጤና የሕዝብ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ ማንኛውም መንግሥት የዜጎቹን ጤና የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ምክንያቱም የአንድ ሰው ህመም ሌሎች ላይም መድረሱ ስለማይቀር።”
ኢቦላ ዓለም አቀፋዊ የጤና ስጋት በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ሁሉም ሀገራት “እጅ ለእጅ ተያይዘው መሥራት አለባቸው” ብለዋል።
“ቀደም ሲል እንደሆነው ሁሉ አሁንም በቆራጥነትና ጥንካሬ በሽታው በቁጥጥር ስር ሆኖና ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ እንደምናይ ተስፋ እናደርጋለን።”
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X