ውህደት ለዩሬዥያ ኢኮኖሚ ኀብረት አባል ሀገራት ተጨባጭ ጥቅሞችን እያስገኘ ነው - ፑቲን

© telegram sputnik_ethiopiaውህደት ለዩሬዥያ ኢኮኖሚ ኀብረት አባል ሀገራት ተጨባጭ ጥቅሞችን እያስገኘ ነው - ፑቲን
ውህደት ለዩሬዥያ ኢኮኖሚ ኀብረት አባል ሀገራት ተጨባጭ ጥቅሞችን እያስገኘ ነው - ፑቲን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2026
ሰብስክራይብ

ውህደት ለዩሬዥያ ኢኮኖሚ ኀብረት አባል ሀገራት ተጨባጭ ጥቅሞችን እያስገኘ ነው - ፑቲን

​የሩሲያ ፕሬዚዳንት በአስታና በተካሄደው የዩሬዥያ ጠቅላይ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ "ኅብረቱ ዕድገቱን ቀጥሏል" ብለዋል።

በፑቲን የተዘረዘሩ የቡድኑ ዋና ዋና ስኬቶች የሚከተሉት ናቸው፦

​◻ በኅብረቱ ውስጥ ለሸቀጦች፣ ለአገልግሎቶች፣ ለካፒታል እና ለሰው ኃይል የሚሆኑ የጋራ ገበያዎች በከፍተኛ ደረጃ ተመስርተዋል፣

​◻ የአባል ሀገራቱ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ አመልካቾች አወንታዊ እንቅስቃሴ እያሳዩ ነው፣

​◻ በአባል ሀገራቱ መካከል የሚደረጉ የንግድ ክፍያዎች በሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሀገር ውስጥ ገንዘቦች እየተከናወኑ ነው፣

​◻ አባል ሀገራቱ በአስፈላጊ የምግብ ምርቶች ራሳቸውን ለመቻል አቅደው እየሠሩ ነው፣

​◻ የቡድኑ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፍላጎትን በመሳቡ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ከኀብረቱ ጋር ለመተባበር ፍላጎታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፣

​◻ የአባል ሀገራቱ የንግድ ልውውጥ እ.ኤ.አ በ2025 95 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፣

​◻ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ለሩሲያ ፍጹም ቀዳሚ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0