ኬንያ አሜሪካ በናይሮቢ ለመገንባት ያቀደችውን የኢቦላ ማገገሚያ ማዕከል አገደች
15:39 29.05.2026 (የተሻሻለ: 15:44 29.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኬንያ አሜሪካ በናይሮቢ ለመገንባት ያቀደችውን የኢቦላ ማገገሚያ ማዕከል አገደች
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ፤ የቀረበው የሕግ ክርክር እልባት እስኪያገኝ ድረስ ከአሜሪካ ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት መንግሥት ለኢቦላ የተጋለጠ ወይም በበሽታው የተያዘ ማንኛውንም ሰው እንዳይቀበል ጌዜያዊ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ክሱ የቀረበው፤ የኢቦላ መለያ ማዕከል የመገንባት ዕቅዱ በምስጢር የተያዘና ተገቢው የሕዝብ ተሳትፎ፣ የፓርላማ ምርመራ ወይም የአስተዳደር ጥበቃዎች አልተደረገበትም በሚል በተሟገትው "ካቲባ ኢንስቲትዩት” ነው።
ማዕከሉ በኬንያ የሚገኙና ለኢቦላ የተጋለጡ የአሜሪካ ዜጎችን ለይቶ ለማቆየት የሚያገለግል ነው ተብሏል። ሗይት ሐውስ የበሽታው ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች አሜሪካ መግባት እንደሚከለከሉ እና ወደ ሌላ ሀገር እንዲዛወሩ እንደሚደረጉ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X