ኢትዮጵያ ዚምባብዌ ውስጥ ስምንት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷን አስታወቀች
15:13 29.05.2026 (የተሻሻለ: 15:34 29.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ዚምባብዌ ውስጥ ስምንት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷን አስታወቀች
ተከላውን በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ስር በሚቀጥለው ዓመት ለማካሄድ መታቀዱን በዚምቧቤ የኢትዮጵያ አምባሳደር ራሺድ መሐመድ ገልፀዋል።
ተነሳሽነቱን በመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የጋራ ትብብር በትንሹ 4 ሚሊዮን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በማሳተፍ ለማከናወን መታሰቡንም አስታውቀዋል።
“ይህ ተነሳሽነት ለአየር ንብረት ለውጥ ለማትበገር እና ለአረንጓዴ ዚምቧቤ መንገድ ይጠርጋል" ብለዋል።
ተንቀሳቃሽ ምሥሉ “በመትከል ማንሠራራት” በሚል መሪ ሀሳብ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት በተገኙበት የተካሄደውን የ2017ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X