ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

© telegram sputnik_ethiopiaጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2026
ሰብስክራይብ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

ፊርማው በመጀመሪያው የብራዚል-አፍሪካ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጉባኤ ላይ እንደተፈረመ ታውቋል፡፡

ስምምነቱ የሚከተሉትን ስትራቴጂካዊ ዘርፎች አካቷል፦

◾ግብርና፣

◾ሕክምና፣

◾ሰብዓዊ ሳይንስ፣

◾ቴክኖሎጂና ሰው ሠራሽ አስተውህሎት፣

◾ኢነርጂ።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና፣ ምርምር እና የማኅበረሰብ አገልግሎትን በማቀናጀት ፈር ቀዳጅ የሆነውን “ማኅበረሰብ-ተኮር ትምህርት” ፍልስፍና በጉባዔው ላይ እንዳቀረበ እና የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴሉን ለመተግበር ጠንካራ ፍላጎት እንዳሳዩ አስታውቋል።

በብራዚል የትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ ጉባኤ፤ ከ70 የብራዚል ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችና እና ከ64 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዘጠኝ የብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0