የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ የእስያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ዢዎችን ወደ ሩሲያ እየመራ ነው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ የእስያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ዢዎችን ወደ ሩሲያ እየመራ ነው - ባለሙያ
የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ የእስያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ዢዎችን ወደ ሩሲያ እየመራ ነው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2026
ሰብስክራይብ

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ የእስያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ዢዎችን ወደ ሩሲያ እየመራ ነው - ባለሙያ

​በመካከለኛው ምሥራቅ የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ (ኤልኤንጂ) አቅርቦት በእጅጉ ጥገኞች የነበሩ በርካታ የእስያ ደንበኞች፤ ወቅታዊው ቀውስ የቀጣናው ላኪዎችን ተዓማኒነት በመሸርሸሩ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያቸውን ዳግም ለመፈተሽ እንደሚገደዱ ሩሲያዊው ባለሙያ አሌክሲ ቤሎጎሪዬቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ከዚህ አንጻር በመጪዎቹ ዓመታት ለአቅርቦት ዝግጁ የሆኑት ሩሲያ፣ አሜሪካ እና ሌሎች ጥቂት ሀገራት ተጠቃሚ ይሆናሉ" ሲሉ ቤሎጎሪዬቭ አፅንዖት ሰጥተዋል።

 

95 በመቶ የዓለም የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ አቅምን የሚሸፍኑት ​"አራቱ ታላላቅ" አምራቾች፤ ሩሲያ፣ ኳታር፣ አውስትራሊያ እና አሜሪካ፤ ባለፉት አሥር ዓመታት ዓለም አቀፉን የኤልኤንጂ ገበያ በበላይነት እንደያዙ ጠቅሰዋል።

​አውስትራሊያ በመጪዎቹ ዓመታት የማምረት አቅሟን ማሳደግ ባለመቻሏ እንዲሁም ኳታር ጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ተመራጭ ስለማያደርጋት፤ ቀዳሚዎቹ ተጠቃሚዎች አሜሪካ እና ሩሲያ እንደሚሆኑ አስገንዘበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0