ኢትዮጵያ ከገቢዋ 26 በመቶውን ለዕዳ ክፍያ እንደምታውል የአፍሪካ ልማት ባንክ ይፋ አደረገ
18:42 28.05.2026 (የተሻሻለ: 18:44 28.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከገቢዋ 26 በመቶውን ለዕዳ ክፍያ እንደምታውል የአፍሪካ ልማት ባንክ ይፋ አደረገ
የአኅጉሪቱ የገንዘብ ተቋም ይህን ያለው “በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንበያ 2026” ሪፖርቱ ሲሆን የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከወጪ ንግዷ በ220 በመቶ እንደሚበልጥ እና አጠቃላይ የሕዝብ ዕዳዋ ደግሞ ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት 42.8 በመቶ እንደሚሆን ገልጿል።
በተጨማሪም ከዩሮቦንድ አበዳሪዎች ጋር በዕዳ ሽግሽግ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር ፍሬ አለማፍራቱ ዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያዎችን እንዳታገኝ ማነቆ መሆኑን ባንኩ አመልክቷል።
ሆኖም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እነዚህን ተግዳሮቶች በመቋቋም እ.አ.አ 2025/26 7.8 በመቶ፤ በ2026/27 ደግሞ 8.5 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል።
ባንኩ ለዚህ ዕድገት አቀጣጣይ ናቸው ያላቸውን ቁልፍ ነጥቦችም ጠቅሷል፦
የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣
የሚጠበቁ የዕዳ ሽግሽጎች፣
የውስጣዊ ግጭቶች መርገብ፣
አዲስ የውጭ የገንዘብ ድጋፎች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X