ካሜሩን እስከ 2035 ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ምጣኔዋን ከ30 በመቶ በላይ ለማሳደግ እና የጥሬ ዕቃ ግዢን ለመቀነስ አቅዳለች - ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopiaካሜሩን እስከ 2035 ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ምጣኔዋን ከ30 በመቶ በላይ ለማሳደግ እና የጥሬ ዕቃ ግዢን ለመቀነስ አቅዳለች - ባለሥልጣን
ካሜሩን እስከ 2035 ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ምጣኔዋን ከ30 በመቶ በላይ ለማሳደግ እና የጥሬ ዕቃ ግዢን ለመቀነስ አቅዳለች - ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.05.2026
ሰብስክራይብ

ካሜሩን እስከ 2035 ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ምጣኔዋን ከ30 በመቶ በላይ ለማሳደግ እና የጥሬ ዕቃ ግዢን ለመቀነስ አቅዳለች - ባለሥልጣን

​ ካሜሩን "ጥሬ ዕቃውም ሆነ ገበያው" ስላላት ቆሻሻን ወደ ንግድ ሀብት መለወጥ ትችላለች ሲሉ የካሜሩን የተፈጥሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂ ልማት ጥምረት ፕሬዝዳንት ፍራንክ ሩሰል አቴባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

​እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ ብሔራዊ ዕቅዱ በትኩረት የሚሠራባቸው አራት ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው፡-

​🟠 የግብርና-ኢንዱስትሪ፣

🟠 የፕላስቲክ ቆሻሻ፣

🟠 የደን ልማት፣

🟠 የዕንጨት ሥራ።

አገልግሎት የሰጠ ፕላስቲክን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል የድንጋይ ንጣፎችን እና ቧንቧዎችን የማምረት ሥራዎች ከወዲሁ እየተከናወኑ እንደሚገኙ አቴባ ጠቁመዋል።

​“ተፈጥሯዊ ቆሻሻ ከጠቅላላው ቆሻሻችን 60 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናል፤ ይህንን ደግሞ ወደ ማዳበሪያና ባዮጋዝ መቀየር ይቻላል።”

​ የካሜሩን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ምጣኔ አሁን ላይ ከ10 በመቶ በታች መሆኑን የገለጹት አቴባ፤ የቆሻሻ ማቀነባበር ሥራን ለማስፋፋት የሚደረጉ ጥረቶች እ.ኤ.አ እስከ 2035 ድረስ 300 በመልሶ ማልማት-ኢኮኖሚ ላይ የሚሠ ሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠርና ለማደራጀት ከተያዘው ዕቅድ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0