በኢትዮጵያ የተገኙ 100 ሺህ ዓመታትን ያስቆጠሩ አጥንቶች ቀደምት የአስከሬን ማቃጠል ልማዶችን አመላከቱ
17:51 28.05.2026 (የተሻሻለ: 18:44 28.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የተገኙ 100 ሺህ ዓመታትን ያስቆጠሩ አጥንቶች ቀደምት የአስከሬን ማቃጠል ልማዶችን አመላከቱ
ቅሪተ አካላቱ የተገኙት በአፋር ክልል በመካከለኛው አዋሽ የምርምር ቦታ ከፋሮ ዳባ ደለል ውስጥ ነው፡፡ 100 ሺህ ዓመታት የተገመቱት ግኝቶች የእንስሳት ቅሪተ አካላት፣ የድንጋይ መሣሪያዎች እና ቢያንስ የሦስት ሆሞ ሳፒያንስ ከፊል አጽሞችን ያካተቱ ናቸው።
ተመራማሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት መጠን የተጋለጡ የሰው አጥንቶችንም አግኝተዋል።
በመንጋጋ ጥርስ እና በአቅራቢያው ባሉ የአጥንት ቁርጥራጮች ላይ የቃጠሎ ምልክቶች እንደተገኙ የፊንላንድ ዑውሉ ዩኒቨርስቲ አጥኚዎች ተናግረዋል፡፡ በአጥንቶቹ ላይ የደረሰው ጉዳት በዘመናዊ ፎረንሲክ ሳይንስ ሆን ተብሎ የተቃጠለ ነው የሚያስብሉ ከፍተኛ የቃጠሎ ምልክቶች ማለትም የመሰንጠቅ፣ የማረር፣ የቀለም መቀየር እና ስብራቶች እንደታዩ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
ጥናቱ ከተረጋገጠ የአስከሬን ማቃጠል ልማድን በአስር ሺህዎች ዓመታት ወደኋላ የሚመልስ እና ሆሞ ሳፒየኖች በአፍሪካ ብቻ በሚኖሩበት ዘመን ይከናወን እንደነበር የሚጠቁም ይሆናል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X