የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር "ሕያው ቃል ኪዳን ነው" - ላይቤሪያ ለአንድነት፣ እኩልነት እና የጋራ ኃላፊነት ጥሪ አቀረበች
16:54 28.05.2026 (የተሻሻለ: 17:04 28.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር "ሕያው ቃል ኪዳን ነው" - ላይቤሪያ ለአንድነት፣ እኩልነት እና የጋራ ኃላፊነት ጥሪ አቀረበች
የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎ ኛንቲ፤ ቻይና በጠራችው የተመድ የውይይት መድረክ ላይ የተደረገውን "ወቅቱን የጠበቀ" ክርክር ያደነቁ ሲሆን የትኛውም ሀገር በብቸኛ የበላይነት ሌሎችን እንዳሻው ሊያደርግ አይገባም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የድርጅቱ ቻርተር በክፍፍል እና ሕግን መርጦ በመተግበር "ውጥረት ውስጥ" ወድቋል ሲሉ ያስጠነቀቁት ሚኒስትሯ፤ በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ የሚታዩ አምባገነናዊነቶችን በመንቀፍ፤ የሁሉም ሀገራት የእኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ከላይቤሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ተሞክሮ በመነሳት፤ በድህነት፣ በእኩልነት እጦት እና በሀብት ብክነት ላይ የተቀናጀ የጋራ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X