ዘለንስኪ በምንም መልኩ ሂትለር ላይ ባይደርስም በሦስተኛ ተርታ ፊልም ገፀ-ባህሪውን መጫወት ይችላል - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ

© telegram sputnik_ethiopiaዘለንስኪ በምንም መልኩ ሂትለር ላይ ባይደርስም በሦስተኛ ተርታ ፊልም ገፀ-ባህሪውን መጫወት ይችላል - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ
ዘለንስኪ በምንም መልኩ ሂትለር ላይ ባይደርስም በሦስተኛ ተርታ ፊልም ገፀ-ባህሪውን መጫወት ይችላል - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.05.2026
ሰብስክራይብ

ዘለንስኪ በምንም መልኩ ሂትለር ላይ ባይደርስም በሦስተኛ ተርታ ፊልም ገፀ-ባህሪውን መጫወት ይችላል - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ

 

ሰርጌ ናሪሽኪን በዓለም አቀፉ የደህንነት ፎረም ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​▪ በርካታ የዘመናችን ፖለቲከኞች ገንቢ ድርድሮችን የማካሄድ ብቃታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን እያሳዩ ነው፣

​▪ አውሮፓ የዓለም አቀፍ ግጭት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰች ነው፣

​▪ የአውሮፓ ኅብረት በከፍተኛ ሁኔታ እየታጠቀ ባለበት ወቅት የጦርነት "ጉሰማ" በተለይ በአውሮፓ አይሎ እየተደመጠ ነው፣

​▪ የአውሮፓ ልሂቃን የዩክሬን ግጭትን በተቻለ መጠን በማራዘም ተጠቃሚ ለመሆን ይፈልጋሉ፣

​▪ አውሮፓውያን ሩሲያ የዩክሬን ግጭትን ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት ለማክሸፍ ይሞክራሉ፣

​▪ የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬንን ከሩሲያ ጋር በማጋጨት በመሠረታዊነት "አዳክመዋታል"፣

​▪ ለዘለንስኪ የሚደረገው ድጋፍ ለአውሮፓውያን ከጊዜ ወደ ጊዜ ውድ እየሆነ ከመምጣቱ በላይ ለማኅበራዊ ውጥረቶች መንስኤ እየሆነ ነው፣

​▪ የአውሮፓ ኅብረት የኪየቭ ጁንታ የሚፈጽማቸውን ጭካኔዎች ሆን ብሎ ያልፋል፣

​▪ የአውሮፓ ዋና ዋና ኃይሎች ያጡትን ኪሳራ ሩሲያን በመዝረፍ ለመመለስ የከንቱ ቅዠት ሰንቀዋል፣

​▪ ከዩክሬን የሚወጡ የጦር መሣሪያዎች በአውሮፓ ያለገደብ ከመዘዋወር ባለፈ በአሸባሪዎች እጅ ይገባሉ፣

​▪ ኔቶ በምስራቃዊ ክንፉ ወታደራዊ አቅሙን ቀስ በቀስ እያሳደገ ነው፣

​▪ እንግሊዝ የአኅጉሪቱ አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንዲገቡ እየገፋፋች ነው፣

​▪ ኔቶ "በምስራቅ" በኩል ለመጠነ-ሰፊ ግጭት እየተዘጋጀ ይገኛል፣

​▪ የኒውክሌር ጦርነትን የመከላከል ዘመን ገና አልተጀመረም፣

​▪ ዓለም ለረጅም ጊዜ አትረጋጋም፤ ይህ የለውጥ ዘመን ነው፤ "ሰላም ለእኛ ህልም ብቻ ነው"፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0