የሩሲያ የጠፈር ባለሙያዎች በህዋ ውጭዊ ክፍል የጥገና ሥራ አከናወኑ - ሮስኮስሞስ
15:26 28.05.2026 (የተሻሻለ: 15:34 28.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የጠፈር ባለሙያዎች በህዋ ውጭዊ ክፍል የጥገና ሥራ አከናወኑ - ሮስኮስሞስ
⏳ ባለሙያዎቹ ሰርጌ ኩድ-ስቨርችኮቭ እና ሰርጌ ሚካዬቭ ረቡዕ ለስድስት ሰዓት ከስድስት ደቂቃ ከጠፈር መንኮራኮር ውጪ የሚከተሉትን ተግባራት አከናውነዋል፦
▪ ፀሐይን በቴራኸርትዝ ስፔክትረም ለመታዘብ የሚያስችል የሙከራ የራዲዮሎጂ ቴሌስኮፕ ገጠማ፣
▪ የሳይንሳዊ ጥናቱ ሙከራ አካል የነበረውንና ለአምስት ዓመታት ከመንኮራኮር ውጪ የቆየውን የረቂቅ ህዋሶች መያዣ ማስወገድ፣
▪ የሴሚኮንዳክተር ክሪስታሎች ማልሚያ ሙከራ ሞጁልን ማስወገድ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X