ፑቲን እና የካዛክስታን አቻቸው በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ዙሪያ ስምምነት ተፈራረሙ
13:59 28.05.2026 (የተሻሻለ: 14:04 28.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን እና የካዛክስታን አቻቸው በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ዙሪያ ስምምነት ተፈራረሙ
መሪዎቹ የሩሲያ-ካዛክ ስልታዊ ጥምረት ሰባት ምሠሦዎች ሰነድን ጨምሮ በርካታ የጋራ ስምምነቶችን ፈርመዋል።
ሰባቱ ምሠሦዎች የሚከተሉት ናቸው፦
🟠 የጋራ ታሪክ እና ተጨባጭ አረዳዱን በኃላፊነት መያዝ፣
🟠 የዩሬዥያ ውህደትን ለማሳደግ የጋራ ጥረቶችን ማድረግ፣
🟠 የጋራ ድንበርን የመልካም ጉርብትና መንጸባረቂያ ስፍራ ማድረግ፣
🟠 ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን ማጠናከር፣
🟠 የቋንቋ እና የባሕል ብዝሃነትን እንደ የጋራ ቅርስ፣ ባሕላዊ እሴቶች እና የሥልጣኔ ትስስር መውሰድ፣
🟠 የወጣቶች፣ የትምህርት ልውውጦች እና የስፖርት ትብብርን ማሳደግ፣
🟠 ለመጪው ጊዜ የጋራ ራዕይ መቅረፅ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X