ኪየቭ በአፍሪካ ለዘመናዊው የምዕራባውያን ቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ ቀንደኛ አስፈጻሚ ሆና እየሠራች ነው - የሩሲያ ደኅንነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ

© telegram sputnik_ethiopiaኪየቭ በአፍሪካ ለዘመናዊው የምዕራባውያን ቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ ቀንደኛ አስፈጻሚ ሆና እየሠራች ነው - የሩሲያ ደኅንነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ
ኪየቭ በአፍሪካ ለዘመናዊው የምዕራባውያን ቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ ቀንደኛ አስፈጻሚ ሆና እየሠራች ነው - የሩሲያ ደኅንነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.05.2026
ሰብስክራይብ

ኪየቭ በአፍሪካ ለዘመናዊው የምዕራባውያን ቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ ቀንደኛ አስፈጻሚ ሆና እየሠራች ነው - የሩሲያ ደኅንነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ

​

“በአፍሪካ አኅጉር የሽብርተኝነት ስጋት በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በዚህ ውስጥ ደግሞ የዩክሬን ሚና በግልጽ የሚታወቅ ነው” ሲሉ ሰርጌ ሾይጉ ከዓለም አቀፉ የደኅንነት ፎረም ጎን ለጎን ተናግረዋል።

​ ኪየቭ ተመድ የባሪያ ንግድ እና ዘርን መሠረት ያደረገ የአፍሪካውያን ባርነት በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ብሎ በፈረጀበት የመጋቢት 16ቱ የድምጽ አሰጣጥ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጓን በምሳሌነት አንስተዋል።

​“ይህ እርምጃ የናዚው ሥርዓት በቀድሞ ቅኝ ገዥ ሀገራት ለሚወከሉት ምዕራባውያን አስተዳዳሪዎቹ ላይ ጥገኛ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል” ሲሉም አክለዋል።

​ አፍሪካውያንን በተመለከተ የኪየቭ እባባምነት ማሳያ በሰሜናዊ ማሊ ቲንዛዋተን አቅራቢያ በተከሰተው እና የማሊ ጦር በቱዋሬግ ተገንጣዮች እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ባለው ጅኒም* ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ጥቃት ላይ እጄ አለበት ብላ ማመኗ ነው ሲሉ ሾይጉ ጨምረው ገልጸዋል።

 

​*በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0