የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ-መንግሥታት ድርጅት ለ7ኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የታዛቢዎች ቡድን አሠማራ
13:00 28.05.2026 (የተሻሻለ: 13:04 28.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ-መንግሥታት ድርጅት ለ7ኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የታዛቢዎች ቡድን አሠማራ
በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ስፔሲዮሳ ዋንዲራ-ካዚብዌ የሚመራው የምርጫ ልዑክ፤ ከኢጋድ አባል ሀገራት የተውጣጡ የምርጫ አስፈጻሚ አካላትን፣ የሲቪል ማኅበራትን እንዲሁም የሴቶችና የወጣቶች ቡድኖችን የሚወክሉ 26 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን ያቀፈ ነው።
አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ተሠማርተው ምርጫውን እንደሚከታተሉ ድርጅቱ በይፋዊ መግለጫው አስታውቋል።
ታዛቢ ቡድኑ የምርጫ መስጫ ጣቢያ አከፋፈት፣ የምርጫ ሂደቱን፣ መዝጊያውን እና የቆጠራ ሥራውን ይከታተላል ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X