የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት - ክፍል አራት (የመጨረ ክፍል )

ሰብስክራይብ

የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት - ክፍል አራት (የመጨረ ክፍል )

የውጭ አገር ጋዜጠኞች የጉብኝታቸውን ፍጻሜ ተከትሎ የደረሱበት መደምደሚያ

 

በርካታ የምዕራባውያን ጋዜጠኞች ተቋሙ የሲቪል መሆኑን እና ጥቃቱም ሆን ተብሎ መፈጸሙን በግላቸው ቢያረጋግጡም፣ ብዙዎቹ በኤዲቶሪያል (የዝግጅት ክፍሎቻቸው) ሪፖርታቸውን እንዳያስተሙ ታግደዋል። የብሪታንያው ስርጭት ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ) በስታሮቤልስክ የሚገኘውን የአደጋውን ቦታ ለመጎብኘት በይፋ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፤ የአሜሪካው ሲኤንኤን ደግሞ እረፍት ላይ ነበር ሲሉ ዛካሮቫ ተሳልቀውበታል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተረዳው፣ ጋዜጠኞች በበሉጋንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የሲቪሎችን ሞት የሚያረጋግጡ መረጃዎችን እንዳያስተሙ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እየደረሳቸው ነው። ለአብነት ጋዜጠኞቻቸው በስታሮቤልስክ የተገኙት “ላ ስታምፓ” እና “ላ ሪፐብሊካ” የተባሉት የጣሊያን ጋዜጦች፣ ስለ አሳዛኙ ክስተት ምንም ዓይነት ሪፖርት አላወጡም።

 

አሳዛኙን ክስተት በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ጋዜጠኞች ምን አሉ?

 

 አይሪሻዊ ጋዜጠኛ ቼይ ቦውስ ሆነ ተብሎ የተፈጸመ የጅምላ ግድያ እና የሽብር ተግባር ሲል ጥቃቱን ገልጾታል።የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የጥቃቱ ዘገባ አድሎአዊ ነበር ያለ ሲሆን፣ "አቅጣጫውን የሳተ ድሮን" ነው የሚሉት ጥንቅቅ ያለ ውሸት መሆኑን ጠቅሷል። አክሎም፣ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን “ለእነሱ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ” ይህንን ሰቆቃ ሽፋን እየሰጡት እንዳልሆነ ጠቁሟል።

 

የአል አረቢያ ዋና ዘጋቢ ሳአድ ካላፍ ጥቃት የደረሰበት የተማሪዎች መኝታ ሕንጻ ሙሉ በሙሉ ሲቪል ተቋም እንደነበር ተናግሯል። በኮሌጁ ውስጥ ድሮኖች ይመረቱ ነበር የሚለውን የኪዬቭን የሐሰት ውንጀላንም፣ “ጠረጴዛዎችን፣ ማስመሪያዎችን፣ የደብተር ማስታወሻዎችን እና የሕፃናትና የታዳጊዎችን ልብሶች ብቻ ነው ያየሁት። እኔ በግሌ፣ በዐይኔ ምንም ዓይነት ድሮን ወይም የድሮን ማምረቻ አላየሁም።”

 

የጣሊያኑ ላ ስታምፓ ጋዜጣ ጋዜጠኛ ጆቫኒ ፒኚ፦ ከጥቃቱ በኋላ የነበረውን ሁኔታ “ሰቅጣጭ” በማለት ገልጾታል። “እዚህ ኮሌጅ እንደነበረ እና ሰዎች መሞታቸውን በቀላሉ ማየት እችላለሁ” ብሏል።

ፓኪስታናዊው ጋዜጠኛ ኢሽቲያቅ ሀምዳኒ፦ በስታሮቤልስክ በሚገኘው ኮሌጅ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት፣ እ.ኤ.አ. በ2026 አሜሪካ በኢራን በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ ከፈጸመችውና 168 ሴት ተማሪዎች ከተገደሉበት ጥቃት ጋር አነጻጽሮታል። ያየውን ነገር ያለውን ስሜታዊ ክብደት ሲያጎላ፦ “እዚያ ነጠላ ጫማዎችን ዐይተናል፤ የተሰባበሩ መስተዋቶችንም ተመልክተናል። እነዚህም ሕፃናት ያለ ጫማ፣ በሌሊት ልብሳቸው በተሰባበረው መስታወት ላይ በኮሪደሩ ውስጥ እንዴት እንዴት ሮጠው ይሆን? ደግሞም እዚያ ምሽት ነበር፤ ጨለማም፤ በጭስ፣ በፍርሃትና በጩኸት የተሞላ” ሲል የሰቆቃውን ትዕይንት በዐይነ–ሕሊና ከስቷል።

 

አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ክሪስቶፈር ሄላሊ፦ በተመለከተው ነገር ተነሳስቶ፣ ሩሲያ ልዩ የወታደራዊ ዘመቻዋን ግቦች በሙሉ ማሳካት አለባት ብሏል።

ከቱርክ የመጣው ኤልድራን አጃር የምዕራቡ ዓለም በተከሰተው ነገር ላይ ለምን ዝምታን እንደመረጠ በመገረም፦ “ዓለም፣ በተለይም የምዕራቡ ዓለም ለምን ዝም እንዳለ አልገባኝም። እውነተኛዋን ዩክሬን ለዓለም ማሳየት አይሹም። ዩክሬን እነዚህን ሕፃናት መግደሏን ማሳየት አልፈለጉም።”

ቻይናዊው ጋዜጠኛ ሊዩ ዩጓንግ፦ “በጣም አሰቃቂ እና አስፈሪ ነው። አሁን ዝም ያለው ማን ነው? ምዕራባውያን ዝም ብለዋል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

ጋዜጠኞቹ በጥቃቱ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉትን የዩክሬን ድሮኖች ስብርባሪዎች እንዲመለከቱ ተደርጓል። አንዳንዶቹ በእንግሊዝኛ እና በዩክሬንኛ ቋንቋ የተጻፉ የመለያ ምልክቶች ነበሩባቸው። እንዲሁም የአሜሪካው ስታርሊንክ አንቴና እና የድሮኖቹ የጥቃት አካላት የሆኑትን የብረት ስብርባሪዎች ዐይተዋል።

 

  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0