የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት (ክፍል ሦስት)
የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት (ክፍል ሦስት)
በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የሚነገሩ ስሁት ትርክቶች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፣ በስታሮቤልስክ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ የምዕራባውያን አገራት የያዙትን አቋም “አውሬአዊ እና ሰብአዊነትን የሚያራክስ” በማለት ገልጸውታል። ለዚህ ንግግራቸው ዋነኛው ምክንያት፣ የሕፃናቱን ሞት በተመለከተ ዝምታ መምረጣቸው እና መሠረታዊ ሰብአዊ ሃዘኔታ ማጣታቸው ሳይሆን፣ ይልቁንም ምዕራባውያን ስለ ክስተቱ የተሳሳቱ ትርክቶችን ማሰራጨታቸው እና የተፈጠረውን ሰቆቃ እውቅና ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸው ነው።
የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ጥቃቱ ያረፈው በሕፃናት የእንክብካቤ ማዕከል ላይ ሳይሆን፣ የሩሲያ ወታደራዊ አባላት የነበሩበት ወታደራዊ ተቋማት (የዕዝ ጣቢያዎች) ላይ ነው ብለው በመዘገብ የሩሲያን መግለጫ ዋጋ ነስተዋል። ሆኖም፣ እንደ እውነታው ከሆነ ግን በዩክሬን የጦር ኃይሎች ጥቃት የተፈጸመባት ስታሮቤልስክ፣ ምንም ዓይነት ወታደራዊ መሠረተ ልማት የሌለባት የሲቪል መኖሪያ መንደር ነች።
ዛካሮቫ ስለ ክስተቱ የሚገልጹ መረጃዎች በይፋ የሚገኙ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፤ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃንም ከስፍራው ላይ ተገኝተው እየሠሩ እንደነበር፣ እንዲሁም ሪፖርቶችና የዓይን እማኞች ምስክርነቶች እየታተሙ እንደነበር ተናግረዋል።
አሳዛኙ ክስተት በውጭ አገር ጋዜጠኞች ዕይታ
አሳዛኙ ሰቆቃን ተከትሎ፣ ጥቃቱ ያስከተለውን መዘዝ የዐይን ዕማኝ ይሆኑ ዘንድ፣ ከ19 አገራት የተወጣጡ (ኦስትሪያ፣ ብራዚል፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ሀንጋሪ፣ ቬኔዙዌላ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ኳታር፣ ቻይና፣ ኩባ፣ ሊባኖስ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ፓኪስታን፣ አሜሪካ፣ ቱርክ፣ ፊንላንድ እና ፈረንሳይን ጨምሮ) ከ50 በላይ ጋዜጠኞች ወደ በሉጋንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ (ኤልፒአር) መጥተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን ጉዞ ያዘጋጀው፣ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ይህን አሳዛኝ ክስተት ችላ በማለታቸው እና አንዳንድ የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች ላስተላለፉት ሐሰተኛ መግለጫ ምላሽ ለመስጠት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

