የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ተልዕኮ 7ኛውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገባ - ሕብረቱ
17:44 27.05.2026 (የተሻሻለ: 17:54 27.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ተልዕኮ 7ኛውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገባ - ሕብረቱ
የአፍሪካ ሕብረት በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ መሠረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራ የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን አስታውቋል።
ልዑኩ 61 በመቶ ያህሉ ሴቶች የሆኑና ከ37 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ አምባሳደሮችን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የሲቪል ማኅበራት አባላትን፣ የሰብዓዊ መብትና የሚዲያ ባለሙያዎችን እንዲሁም የወጣቶች ድርጅት ተወካዮችን ያካተቱ 73 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን የያዘ ነው።
ታዛቢዎቹ በምርጫው ዕለት ድምፅ አሰጣጥንና የቆጠራ ሂደቶችን ለመታዘብ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚሰማሩ ሲሆን፤ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሚዲያ አካላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ሥራቸውን ያከናውናሉ ተብሏል።
⏳ ቡድኑ በምርጫው ሂደት ላይ ያለውን የመጀመሪያ ደረጃ የግምገማ መግለጫ ግንቦት 26 ቀን በስካይላይት ሆቴል በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ ሙሉና ዝርዝር ሪፖርቱን ደግሞ ምርጫው ከተጠናቀቀ ከሁለት ወራት በኋላ እንደሚያወጣ ይፋ አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X