የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት (ክፍል አንድ)
16:44 27.05.2026 (የተሻሻለ: 16:54 27.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዩክሬን ጦር ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የፈፀመው ጥቃት (ክፍል አንድ)
እ.ኤ.አ. ግንቦት 22 ቀን 2026 (14/9/2018 ዓ.ም.) እኩለ ሌሊት ላይ፣ የዩክሬን ጦር ኃይሎች በሉጋንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ስታሮቤልስክ ከተማ በሚገኘውና የሉጋንስክ የሥነ–ትምሕርት ዩኒቨርሲቲ አካል በሆነው በስታሮቤልስክ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተማሪዎች መኝታ ክፍል እና የመማሪያ ሕንጻ ላይ ጥቃት ፈጽሟል። በዚህ አስከፊ ጥቃት ምክንያት 21 ወጣቶች ሲገደሉ፣ ሌሎች 65 ታዳጊዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ ያለው የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የክስተቶቹ ቅደም-ተከተል
1⃣ ከሌሊቱ 8 ሠዓት ገደማ ጥቃቱ ተጀመረ። ሶስት ተከታታይ የድሮን ጥቃቶች ሕንጻውን ተራ በተራ መተውታል።
2⃣ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ዕድሜያቸው በ14 እና 18 መካከል የሚገኙ 86 ተማሪዎች ነበሩ።
3⃣የድሮን ጥቃቶቹ ተከትሎ የሕንጻው አብላጫው ክፍል ተደርምሷል።
4⃣የነፍስ አድን ስራው ለተከታታይ ቀናት የቀጠለ ሲሆን፣ የተጎዱትን እና የሞቱትን ሰዎችን ለማውጣት ፍርስራሾች ተነስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X