የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሔት "የዓመቱ ምርጥ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ" አሸናፊ ሆኑ
15:05 27.05.2026 (የተሻሻለ: 15:14 27.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሔት "የዓመቱ ምርጥ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ" አሸናፊ ሆኑ
መጽሔቱ የ2026 የላቀ የአፍሪካ ቢዝነስ መሪዎች ሽልማት አሸናፊዎችን ይፋ ባደረገበት ወቅት፤ ኢትዮጵያዊው እዮብ ተካልኝ "የዓመቱ ምርጥ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ"፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ "የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ብራንድ" በመሆን መመረጣቸውን አስታውቋል።
እዮብ ተካልኝ ከታንዛኒያው አማኑኤል ቱቱባ ጋር በመሆን የዘርፉን የቀዳሚነት ክብር ተቀዳጅተዋል።
በሕዝብ ድምፅና በተቋማዊ ምዘና አሸናፊ የሆኑት እነዚህ የኢትዮጵያ ተቋማትና መሪዎች፤ በቀጣዩ ሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም በለንደን በሚካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይፋዊ ክብርና ሽልማታቸውን እንደሚቀበሉ ታውቋል።
እንደ ዳንጎቴ ግሩፕ፣ ማስተርካርድ አፍሪካ እንዲሁም የጋናው የፋይናንስ ሚኒስትር ካሲኤል አቶ ፎርሰን ያሉ ታዋቂ ተቋማትና ግለሰቦች በተለያዩ ዘርፎች ማሸነፋቸው ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia