ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 365.9 ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
20:28 26.05.2026 (የተሻሻለ: 20:34 26.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 365.9 ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ሀገሪቱ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 9 ወራት ውስጥ 24 ሺህ 940 ጊጋ ዋት ሠዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የተጠቀሰውን ገቢ ማግኘት መቻሉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት፦
ከተለያዩ የኃይል ምንጮች 1,669 ሜጋ ዋት አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተችሏል፡፡
የሀገሪቱን አጠቃላይ የማመንጨት አቅም ከ7,910 ሜጋ ዋት ወደ 9,579 ሜጋ ዋት ማሳደግ ተችሏል፡፡
ከውኃ ኃይል ብቻ 1,599 ሜጋ ዋት የኃይል መጠን ተገኝቷል፡፡
27፣401 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኢነርጂ ማምረት ተችሏል፡፡
የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ ከ141.8 ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ 148.6 ሺህ ኪሎ ሜትር አድጓል፡፡
ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የታዳሽ ኃይል እምቅ አቅም በመጠቀም በቀጣናው አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባትና የውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X