በጋሞ ዞን በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የ43 ሚሊዮን ብር የዕርዳታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ
20:14 26.05.2026 (የተሻሻለ: 20:24 26.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በጋሞ ዞን በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የ43 ሚሊዮን ብር የዕርዳታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ
ለአራት ወራት ተግባራዊ የሚሆነውን የማቋቋሚያ ፕሮግራም ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እንዳስታወቀው፦
ለ500 አባወራዎች በየወሩ የ11,350 ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን፣
የንጹሕ ውኃ አቅርቦት ሥርዓትን መልሶ መጠገንን፣
የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ አቅርቦትንና የስነ-ልቦና ድጋፍ አገልግሎቶችን ያካተተ ነው።
⏳ቀደም ሲል ለላንቴ ጤና ጣቢያ የ1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የሕክምና መሣሪያዎችንና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎችን ማድረጉን የጠቆመው ማሕበሩ በዞኑ የረጅም ጊዜ መልሶ ማቋቋም ተግባር ላይ ለመሳተፍ ከዋናው መሥሪያ ቤት ፈቃድ እየጠበቀ መሆኑ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X